Caleb Tesfaye/Tensae Ale/Yeselam Mefleqiya

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ዘማሪ ፡ ካሌብ ፡ ተስፋዬ ርዕስ ፡ የሰላም ፡ መፍለቂያ አልበም ፡ ትንሳኤ ፡ አለ

የሰላም ፡ መፍለቂያ ፡ ምንጭ ፡ ነህ ኢየሱሰ ፡ አንተ ፡ እውነተኛ ዓለም ፡ ለቀጣው ፡ ሰው ፡ ለተጐዳ ፡ መጽናኛ የጠፋን ፡ ፈላጊ ፡ የኃጢአተኛ ፡ ወዳጅ ለበዛው ፡ በደሉ ፡ ጠበቃ ፡ ነህ ፡ አማላጅ

ስንቱ ፡ እረፍት ፡ አጥቶ ፡ ኖረ መስሎት ፡ ብዙ ፡ ሞከረ ለፋ ፡ ወጣ ፡ ገባ ፡ ፈልጐ ፡ አላገኘም ምህረትህ ፡ ቀደመ ፡ ከንቱ ፡ ሆኖ ፡ አልቀረም

የሰላም ፡ መፍለቂያ ፡ ምንጭ ፡ ነህ ኢየሱሰ ፡ አንተ ፡ እውነተኛ ዓለም ፡ ለቀጣው ፡ ሰው ፡ ለተጐዳ ፡ መጽናኛ የጠፋን ፡ ፈላጊ ፡ የኃጢአተኛ ፡ ወዳጅ ለበዛው ፡ በደሉ ፡ ጠበቃ ፡ ነህ ፡ አማላጅ

እምቢ ፡ አሻፈረኝ ፡ ብሎ ሄደ ፡ ቤትህን ፡ ጥሎ

በፍቅር ፡ አባብለህ ፡ መለስከው ፡ ያንን ፡ ሰው አንተን ፡ መሳይ ፡ አባት ፡ ከየት ፡ ነው ፡ እሚገኘው

የሰላም ፡ መፍለቂያ ፡ ምንጭ ፡ ነህ ኢየሱሰ ፡ አንተ ፡ እውነተኛ ዓለም ፡ ለቀጣው ፡ ሰው ፡ ለተጐዳ ፡ መጽናኛ የጠፋን ፡ ፈላጊ ፡ የኃጢአተኛ ፡ ወዳጅ ለበዛው ፡ በደሉ ፡ ጠበቃ ፡ ነህ ፡ አማላጅ

ነፍሱን ፡ ለጠሉት ፡ ሁሉ ፡ ሲል ሰጠ ፡ ተቆጠረ ፡ እንደ ፡ ቂል የሰው ፡ ልጆች ፡ ክፋት ፡ እንዲህ ፡ እየጨመረ ምትክ ፡ ሆኖ ፡ ባይሞት ፡ ምን ፡ ይኮን ፡ ነበረ?

የሰላም ፡ መፍለቂያ ፡ ምንጭ ፡ ነህ ኢየሱሰ ፡ አንተ ፡ እውነተኛ ዓለም ፡ ለቀጣው ፡ ሰው ፡ ለተጐዳ ፡ መጽናኛ የጠፋን ፡ ፈላጊ ፡ የኃጢአተኛ ፡ ወዳጅ ለበዛው ፡ በደሉ ፡ ጠበቃ ፡ ነህ ፡ አማላጅ።