Caleb Tesfaye/Tensae Ale/Sew Liela Liela Sil
ዘማሪ ፡ ካሌብ ፡ ተስፋዬ ርዕስ ፡ ሰው ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሲል አልበም ፡ ትንሳኤ ፡ አለ
አለልኝ ፡ የምልብህ ትምክህቴ ፡ የምመካብህ የድሃ ፡ ቀኜ ፡ ምርኩዝ ፡ ነህ አለኝታ ፡ ነህ ፡ ታኮራለህ ማንም ፡ ባይኖረኝ ፡ ዙሪያዬ ማዶ ፡ ቢሆንም ፡ ጓዳዬ አለሁልህ ፡ የሚል ፡ ቢጠፋ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ተስፋ
ሰው ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሲል ሲኮራ ፡ በእንጀራው እኔ ፡ ግን ፡ ከእጅህ ፡ ነው ጠግቤ ፡ የምበላው (፪x) (ክላሲካል)
ከእሳት ፡ ይልቅ ፡ የበረታ ሰልፌ ፡ ኑሮ ፡ ጥዋት ፡ ማታ ደምህ ፡ ከለላ ፡ ሆኖኝ እንዳይፈጀኝ ፡ ጠብቆኝ ተጠነከክልኝና ባሕሩን ፡ ከፈልከውና ተሻገርኩኝ ፡ ሄድኩኝ ፡ ማዶ ነበር ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ከብዶ
መች ፡ ቀላል ፡ ሆነና ያለፍኩት ፡ ጐዳና ለመኖር ፡ በቃሁኝ በእጅህ ፡ ተያዝኩና (፪x) (ክላሲካ)
ሳየው ፡ ዞሬ ፡ ወደ ፡ ኋላ ባይኖረኝ ፡ የአንተ ፡ ከለላ ተረት ፡ ሆኜ ፡ ቀር ፡ ነበረ ምሕረትህ ፡ በዛ ፡ ጨመረ ከፈተና ፡ መውጫ ፡ ብሩ መኖር ፡ አንተን ፡ እየጠሩ አታሳፍር ፡ መልስ ፡ አለህ ለጭንቅ ፡ ቀን ፡ ደራስህ ፡ ነህ
ከጉድጓድ ፡ ከወጡ ከሞት ፡ ካመለጡ ከዚህ ፡ በላይ ፡ ደስታ ምን ፡ አለና ፡ ጌታ (፪x) (ክላሲካል)
ከእናት ፡ በላይ ፡ እናት ፡ ብልህ ከአባት ፡ በላይ ፡ አባት ፡ ብልህ አይበቃ ፡ ሥም ፡ ቢሰጥህ ከዚህ ፡ ሁሉ ፡ የላክ ፡ ነህ ሳልወድህ ፡ ስለ ፡ ወደድከኝ ሳልመርጥህ ፡ ስለ ፡ መረጥከኝ ንጉሥ ፡ ሆይ ፡ እኔም ፡ ምሥጋና ፡ አለኝ ከነኃጢአቴ ፡ ተቀበልከኝ
ጉድለቴን ፡ የሞላ አንተን ፡ የለ ፡ ሌላ ሞገስ ፡ ማዕረጌ ፡ ነህ ወግ ፡ ያየሁብህ (፪x)