እናመሰግንሃለን (Enamesegnhalen) - ቤተልሔም ፡ ወልዴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ቤተልሔም ፡ ወልዴ
(Bethlehem Wolde)


(Volume)

እረኛዬ (Eregnaye) (Vol. Special)
(እረኛዬ (Eregnaye) (Vol. Special))

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2016)
ቁጥር (Track):

፩ (1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Wolde)

ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን
በዙፋኑ ስርም እንሰግድለታለን
ምስጋናችን በፊቱ ሞገስ ያገኝና
ቀጥ ብሎ ያርግ ዛሬም እንደገና (2x)

እናመሰግንሀለን(6x)

አንተ ስትከብር ጌታ ስትወደስ
ከፍ ከፍ ስትል የሱስ ስትሞገስ
እደሰታለሁ ጥማቴ ይህ ነው
ክብርህንም ሳይ ጌታ እኔ እጠግባለሁ

እናመሰግንሀለን(6x)

እልፍ ምስጋና ጌታ ላንተ እንደገና
እልፍ ዝማሬ የሱስ ላንተ ይሁን ዛሬ
እልፍ ጭብጨባ መቅደስህ ይግባ
እልፍ እልልታ ላንተ ይሁን ጌታ (2x)

እናመሰግንሀለን(6x)

እኛስ በጌታ እግዚብሔር ተደስተናል
ፍቅሩን በሕይወታችን ሲገልጽ አይተናል
እያደነቅነው እናመልካለን
በምስጋና ሁሉም ላይ እንጨምራለን

እናመሰግንሀለን(6x)