From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation
Jump to search
|
|
ቤተልሔም ፡ ተዘራ (Bethelehem Tezera)
|
|
|
|
፪ (2)
|
ተፈፀመ (Tefetseme)
|
| ዓ.ም. (Year):
|
፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2005)
|
| ቁጥር (Track):
|
፲ ፪ (12)
|
| ርዝመት (Len.):
|
5:51
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
|
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች (Albums by Bethelehem Tezera)
|
|
|
ዝም ፡ ብዬ ፡ ሳስብ ፡ ሳሰላስለው
እግዚአብሔር እንዴት ፡ ድንቅ ፡ ነው (፫x)
ዝም ፡ ብዬ ፡ ሳስብ ፡ ሳሰላስለው
እግዚአብሔር እንዴት ፡ ድንቅ ፡ ነው (፫x)
አዝ፦ ምሕረቱን ፡ አስቤ ፡ አቤት ፡ ስል ፡ ፍቅሩ ፡ አለ ፡ ለካ ፡ አሃ
ፍቅሩን ፡ አስቤ ፡ አቤት ፡ ስል ፡ ባርኮቱ ፡ አለ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ለካ
ኧረ ፡ እንዴት ፡ አመስግኜው ፡ ልርካ (፬x)
አልጠፋብሽ ፡ ያለኝ ፡ ከልቤ ፡ ውስጥ ፡ የእግዚአብሔርስ ፡ ፍቅር
አሳዳጊነቱ ፡ አባትነቱ ፡ ከህይወቴ ፡ ጅምር
ትዝታ ፡ አይደለም ፡ እያነሳሁ ፡ ምተርክለት
በርሱ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ እስከ ፡ አሁኗ ፡ ድረስ ፡ ያለሁት (፪x)
የእግዚአብሔር ፡ ምህረት ፡ አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት
ሰው ፡ ወዳድነትህ ፡ አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት
የፍቅሩ ፡ ጥልቀት ፡ አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት
እሩህሩህነትህ ፡ አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት (፪x)
አንድ ፡ ሁለት ፡ ብዬ ፡ ውለታውን ፡ አስቤ ፡ ልቆጥር
ጥፍት ፡ ይለኛል ፡ ከየት ፡ ተነስቼ ፡ እንደምጀምር
ይህ ፡ እንኳን ፡ ቢረዳኝ ፡ ቢነግርልኝ ውስጤን ፡ ቢገልጸው
እንደእግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ የለም ፡ ብዬ ፡ ልደምድመው (፪x)
እንደእግዚአብሔር ፡ የለም ፡ አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት
ቢፈለግ ፡ ዘላለም ፡ አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት
እንደእሱ ፡ የለም ፡ አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት
ቢፈለግ ፡ ዘላለም ፡ አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት (፪x)
አዝ፦ ምሕረቱን ፡ አስቤ ፡ አቤት ፡ ስል ፡ ፍቅሩ ፡ አለ ፡ ለካ ፡ አሃ
ፍቅሩን ፡ አስቤ ፡ አቤት ፡ ስል ፡ ባርኮቱ ፡ አለ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ለካ
ኧረ ፡ እንዴት ፡ አመስግኜው ፡ ልርካ(፬x)
|