From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation
Jump to search
ስለ ፡ ዛሬ ፡ ምን ፡ ታውቂያለሽ ፡ ቢሉኝ
አንድ ፡ ነገር ፡ አንድ ፡ መልስ ፡ አለኝ
በእውነት ፡ በእርግጠኛነት
አለ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቸርነት
ስለ ፡ ነገስ ፡ ምን ፡ ታውቂያለሽ ፡ ቢሉኝ
አንድ ፡ ነገር ፡ አንድ ፡ ዕውቀት ፡ አለኝ
በእውነት ፡ በእርግጠኛነት
አለ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቸርነት
በየማለዳው ፡ የምረዳው
ዕለት ፡ በዕለት ፡ ሚታይ ፡ እውነት (፪x)
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ እንደ ፡ ሌለ
እግዚአብሔር ፡ ቸር ፡ እንደሆነ (፪x)
ቸር ፡ ባይሆን ፡ ባለ ፡ ምህረት
እኔ/አንዷ ፡ ነበርኩ ፡ ከሚጠፉት (፪x)
ለክፉዎችም ፡ ቸር ፡ ለማያመሰግኑት
ለሚወዱትም ፡ ቸር ፡ ለሚያምኑበት (፪x)
ያለጠፋሁት ፡ በምን ፡ ምክንያት
ከቦኝ ፡ እንጂ ፡ የአንተ ፡ ምህረት
እያለፈ ፡ እየተከተለኝ
ክፉዉን ፡ ሁሉ ፡ ጥግ ፡ አስያዘልኝ
የደረስክለት ፡ ያውራ ፡ እስኪ ፡ ያውራ
ደግነትህን ፡ ይመስክር
በአንተ ፡ የቀናለት ፡ አሃ
የሕይወቱ ፡ መስመር (፪x)
ቸር ባትሆን ባለ ምህረት
እኔ/አንዷ ነበርኩ ከሚጠፉት (፪x)
ለክፉዎችም ቸር ለማያመሰግኑህ
ለሚወዱህም ቸር ለሚያምኑብህ (፪x)
አልጣሉኝም ፡ ደጋግ ፡ እጆችህ
ፍቅር ፡ ናቸው ፡ ዛሬም ፡ ዓይኖችህ
ለዘለዓለም ፡ ቤትህ ፡ እኖራለሁ
ወደኸኛል ፡ እስከ ፡ መጨረሻው
የደረስክለት ያውራ እስኪ ያውራ
ደግነትህን ይመስክር
በአንተ የቀናለት አሃ
የሕይወቱ መስመር (፪x)
ቸር ፡ ባትሆን ፡ ባለ ፡ ምህረት
እኔ/አንዷ ፡ ነበርኩ ፡ ከሚጠፉት (፪x)
ለክፉዎችም ፡ ቸር ፡ ለማያመሰግኑህ
ለሚወዱትም ፡ ቸር ፡ ለሚያምኑበህ (፪x)
|