አለው (Alew) - በረከት ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
በረከት ፡ ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

፫
(3)

አልበም
(3)

ዓ.ም. (Year): 2023
ቁጥር (Track):

፩ (1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

አለሁ ፡ በምህረቱ ፡ አለሁ ፡ በይቅርታው (እየማረኝ) አለሁ
አለሁ ፡ ምህረት ፡ አጊንቻለሁ ፡ እኔ ፡ ምን ፡ እሆናለሁ
  አለሁ ፡ ሞቴ ፡ ተሽሯል ፡ አለሁ ፡ ምህረቱ ፡ ገኗል ፡ አለሁ
  አለሁ ፡ ህመሜን ፡ ወስዷል ፡ አለሁ ፡ እኔ ፡ ምን ፡ እሆናለሁ
እነ ፡ ሚካኤል ፡ እነ ፡ ገብርኤል
እነ ፡ ሱራፌል ፡ እነ ፡ ኪሩቤል
በክንፎቻቸው ፡ ተከልለውት
ፊቱ ፡ ሚቆሙለት ፡ አምላክ ፡ የሚሉት
በገራፊዎች ፡ ፊት ፡ ቆመልኝ ፡ እሱ ፡ ግን ፡ ስለ ፡ እኔ
ፍቅር ፡ ግድ ፡ ቢለው ፡ ሊያወጣኝ ፡ ከኃጢያት ፡ ከኩነኔ
ዙፋን ፡ የነበረው ፡ ከሰማይ ፡ ዳዊትን ፡ የረዳ
ተንከራተተልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ከናዝሬት ፡ ይሁዳ
ፍቅሩ ፡ ፈሰሰ ፡ ከምህረት ፡ ደጅ
እግዚአብሔር ፡ ከሰማይ ፡ ሰጠኝ ፡ አንድ ፡ ልጅ
ኑሮዬን ፡ ኑር ፡ አለኝ ፡ የእኔን ፡ ልብሰ ፡ ለበሰ
ቆሻሻ ፡ ሂወቴን ፡ በደሙ ፡ ቀደሰ
    አለሁ ፡ ሞቴ ፡ ተሽሯል...

ይሁን ፡ በምትል ፡ ቃል ፡ ፍጥረትን ፡ የሰራ
ጥበብ ፡ የሻተውን ፡ ጥበብን ፡ ያስወራ
አባቶች ፡ ሲጠሩት ፡ በእሳት ፡ የመለሰ
እረኛው ፡ ዳዊትን ፡ ተናግሮ ፡ ያነገሰ
እንደሚታረድ ፡ በግ ፡ ዝም ፡ አለ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ኢየሱስ
ፍቅርን ፡ የኖረ ፡ በተግባር ፡ የፍቅር ፡ ንጉስ
ምድርን ፡ ያቆመ ፡ በቃሉ ፡ ያላንዳች ፡ ምሶሶ
እሱ ፡ ግን ፡ ዝም ፡ አለ ፡ ሞተልኝ ፡ የእኔን ፡ ውርደት ፡ ለብሶ
  ፍቅሩ ፡ ፈሰሰ...
አለሁ ፡ ሞቴ ፡ ተሽሯል...
አለሁ ፡ በምህረቱ ፡ አለሁ...

አብ ፡ ከላይ ፡ ሆኖ ፡ ለኔ ፡ ራራልኝ ፡ አዘነ
ሊያድነኝ ፡ ሽቶ ፡ አንድ ፡ ልጁ ፡ ላይ ፡ ጨከነ
ፍቅር ፡ ልሂድ ፡ አለ ፡ ታዘዘ ፡ ለአባቱ
ክብሩን ፡ ትቶ ፡ ወርዶ ፡ አዳነኝ ፡ በሞቱ
ፍቅር ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ የለም (8X)