Aster Abebe/Keber Yebeqah Neh/Keber Yebeqah Neh
ዘማሪ ፡ አስቴር ፡ አበበ
ቀድሞም ፡ ክብር ፡ የበቃህ ፡ ነህ
ሞልቶ ፡ የተረፈህ
ተገብቶህ ፡ እንጂ ፡ ማን ፡ ሰጥቶህ ፡ ያውቃል ፡ ስለጎደለህ
አንሶብህ ፡ ምሥጋናና ፡ ክብር
አደባባይ ፡ ወጥተህ ፡ ማትለምን
ኢየሱሴ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ምትደነቅ (፪x)
ቀን ፡ አንድ ፡ ተብሎ ፡ ሳይጀመር
አንተኮ ፡ ስትመለክ ፡ ነበር
ወር ፡ አንድ ፡ ተብሎ ፡ ሳይቆጠር
አንተኮ ፡ ስትመለክ ፡ ነበር
ዓመት ፡ በዓመት ፡ ላይ ፡ ሳይደመር
አንተኮ ፡ ስትመለክ ፡ ነበር
በዘመናት ፡ ዘመን ፡ ሳይጨመር
አንተኮ ፡ ስትመለክ ፡ ነበር
ሳይባል ፡ በመጀመሪያ
ሳትፈጥር ፡ ሰማይና ፡ ምድርን
አዕዋፋት ፡ ባየር ፡ ላይ ፡ ሳይበሩ
ሳትመሰርት ፡ በፊት ፡ ተራሮችን
ገና ፡ ሳታበጅ ፡ ሰውን ፡ በጅህ
ሳይወጣ ፡ እስትንፋስ ፡ ከአፍህ
ሁሉ ፡ ነገር ፡ ምንም ፡ ባዶ ፡ እያለ
ምሥጋናህ ፡ ግን ፡ ሞልቶ ፡ የተረፈ
አዝ
ቀድሞም ፡ ክብር ፡ የበቃህ ፡ ነህ
ሞልቶ ፡ የተረፈህ
ተገብቶህ ፡ እንጂ ፡ ማን ፡ ሰጥቶህ ፡ ያውቃል ፡ ስለጎደለህ
አንሶብህ ፡ ምሥጋናና ፡ ክብር
አደባባይ ፡ ወጥተህ ፡ ማትለምን
ኢየሱሴ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ምትደነቅ (፪x)
ቀን ፡ አንድ ፡ ተብሎ ፡ ሳይጀመር ፡ አንተኮ ፡ ስትመለክ ፡ ነበር
ወር ፡ አንድ ፡ ተብሎ ፡ ሳይቆጠር ፡ አንተኮ ፡ ስትመለክ ፡ ነበር
ዓመት ፡ በዓመት ፡ ላይ ፡ ሳይደመር ፡ አንተኮ ፡ ስትመለክ ፡ ነበር
በዘመናት ፡ ዘመን ፡ ሳይጨመር ፡ አንተኮ ፡ ስትመለክ ፡ ነበር
ሳይባል ፡ በመጀመሪያ ፡ ሳትፈጥር ፡ ሰማይና ፡ ምድርን
አዕዋፋት ፡ ባየር ፡ ላይ ፡ ሳይበሩ ፡ ሳትመሰርት ፡ በፊት ፡ ተራሮችን
ገና ፡ ሳታበጅ ፡ ሰውን ፡ በጅህ ፡ ሳይወጣ ፡ እስትንፋስ ፡ ከአፍህ
ሁሉ ፡ ነገር ፡ ምንም ፡ ባዶ ፡ እያለ ፡ ምሥጋናህ ፡ ግን ፡ ሞልቶ ፡ የተረፈ
ቀድሞም ፡ ክብር ፡ የበቃህ ፡ ነህ ፡ ሞልቶ ፡ የተረፈህ
ተገብቶህ ፡ እንጂ ፡ ማን ፡ ሰጥቶህ ፡ ያውቃል ፡ ስለጎደለህ
አንሶብህ ፡ ምሥጋናና ፡ ክብር
አደባባይ ፡ ወጥተህ ፡ ማትለምን
ኢየሱሴ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ምትደነቅ (፪)