Aster Abebe/Keber Yebeqah Neh/Enkwanem Agegnehegn

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ዘማሪ ፡ አስቴር ፡ አበበ ርዕስ ፡ እንኳንም ፡ አገኘኸኝ አልበም ፡ ክብር ፡ የበቃህ ፡ ነህ

የራቀ ፡ ሰፈሬን ፡ ጠንክሮ ፡ የታጠረ ፡ አጥሬን

ምክንያት ፡ ፈልጎ ፡ ፈጥሮ ፡ የራሱን ፡ ሰበብ

ተቀምጦ ፡ ቆየኝ ፡ ከጉድጓዱ ፡ አጠገብ (፪x)


ሳላውቀው ፡ ማንነቱን ፡ የነፍሴን ፡ መድሃኒት

እንዲህ ፡ እንዲያ ፡ እያልኩኝ ፡ ስደረድር ፡ ምክንያት

ለጥቆ ፡ ገባና ፡ ወደ ፡ ህይወቴ ፡ ባህር

ለራሴው ፡ ነገረኝ ፡ የእራሴን ፡ ሚስጥር

የሚጠጣ ፡ ውሃ ፡ በእኔ ፡ ዘንድ ፡ ፍለጋ

መች ፡ ቆመ ፡ ከደጄ ፡ እራሱን ፡ ሊያረካ

ህይወትን ፡ ሊችረኝ ፡ ከከበቡኝ ፡ ሁሉ

አፋቶ ፡ የእራሱ ፡ አደረገኝ ፡ በፍቅሩ


መስሎኝ ፡ በምድሩ ፡ ሰላምና ፡ እርካታ

ከአንዱ ፡ ተጋብቼ ፡ አንደኛውን ፡ ስፈታ

አይቶ ፡ መባከኔን ፡ በእርግጥ ፡ አዝኖልኛል

በአፉ ፡ ቃል ፡ እፎይታ ፡ ወደ ፡ ቤቴ ፡ ገብቷል


እንኳንም ፡ አገኘኸኝ ፡ አንተ ፡ ወዳጄ

እንኳንም ፡ ቀድመኸኝ ፡ ተገኘህ ፡ ከደጄ

ቢሆንማ ፡ ሌላው

ዛሬን ፡ በአይኔ ፡ ባላየሁ


ቤተ ፡ ዘመድ ፡ ይስማ ፡ ጓደኛ ፡ ጎረቤት

ላፍታም ፡ አልዘገይም ፡ ሳልነግር ፡ ይህን ፡ እውነት ጉዴን ፡ ለነገረኝ ፡ የኋላ ፡ ታሪኬን

ልቤ ፡ እርሱ ፡ ጋር ፡ ቀርቷል ፡ ወስዶልኝ ፡ ሸክሜን


እንኳንም ፡ አገኘኸኝ ፡ አንተ ፡ ወዳጄ

እንኳንም ፡ ቀድመኸኝ ፡ ተገኘህ ፡ ከደጄ

ቢሆንማ ፡ ሌላው

ዛሬን ፡ በአይኔ ፡ ባላየሁ