Addisu Worku/Yemesqelu Feqer/Kemotem Yadenal

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ርዕስ ፡ ከሞትም ፡ ያድናል
ዘማሪ ፡ አዲሱ ፡ ወርቁ
Volume 1
አልበም ፡ ክቡር ፡ ክቡር

በሞት ፡ ጥላ ፡ የሚያድር ፡ በግዞች ፡ ሸለቆ
ጠላት ፡ የሚመታው ፡ አሸምቆ
ከአንበሳው ፡ መንጋጋ ፡ ለጣር ፡ የተጣለ
ነበር ፡ ወገኔ ፡ የቆሰለ

አዝ
ከሞትም ፡ ያድነዋል ፡ ከሞትም ፡ ያድናል
ከሞትም ፡ ያድናል ፡ ኢየሱስ (፪x)

ጌታ ፡ ደርሶለታል ፡ ወንጌል ፡ ልኮለታል
ሰማያዊው ፡ ብርሃን ፡ በርቶለታል
መልዕክተኞች ፡ ወጡ ፡ ጠላትን ፡ ገጠሙ
በመስቀሉ ፡ ጉልበት ፡ ድል ፡ አደረጉት

አዝ
ከሞትም ፡ ያድነዋል ፡ ከሞትም ፡ ያድናል
ከሞትም ፡ ያድናል ፡ ኢየሱስ (፪x)

ዓለምና ፡ ትርፏን ፡ ወደ ፡ ኋላ ፡ ገፍቶ
ከመታወቅ ፡ ይልቅ ፡ መናቅ ፡ መርጦ
ዘሩን ፡ ተሸክሞ ፡ በለቅሶ ፡ የሚዘራ
በደስታ ፡ ያጭዳል ፡ ከአምላክ ፡ ጋራ

አዝ
ከሞትም ፡ ያድነዋል ከሞትም ፡ ያድናል
ከሞትም ፡ ያድናል ፡ ኢየሱስ (፬x)