Addisu Worku/Yemesqelu Feqer/Kebur Kebur

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ብዙ ፡ ሃያላን ፡ ነበሩ
በአምላኬ ፡ ላይ ፡ የተኩራሩ
ቅዱሱን ፡ ሀይል ፡ የተገዳደሩ
ያ ፡ ዝናቸው ፡ አምድ ፡ ለብሶ
ታሪካቸው ፡ ተቀልብሶ
አለ ፡ ጌታ ፡ በላያቸው ፡ ነግሶ

አዝ
ክቡር ፡ ክቡር ፡ ሃያል ፡ ክቡር
ለዘለዓለም ፡ የምትኖር
አምላካችን ፡ እግዚአብሔር (፪x)

ሃብታም ፡ በሃብቱ ፡ ይኮራል
ሃያል ፡ በኃይሉ ፡ ይመካል
ስልጣን ፡ ያለው ፡ ጭቁኑን ፡ ይንቃል
ነገር ፡ ግን ፡ ቅኑ ፡ ፈራጅ ፡ ከላይ
ተቀምጧል ፡ ከዙፋን ፡ ላይ
ክንደ ፡ ብርቱ ፡ ጻድቁ ፡ ኤልሻዳይ

አዝ
ክቡር ፡ ክቡር ፡ ሃያል ፡ ክቡር
ለዘለዓለም ፡ የምትኖር
አምላካችን ፡ እግዚአብሔር (፪x)

የመከራ ፡ ወንዝ ፡ ሲሞላ
የጐበዝ ፡ ወኔ ፡ ሲላላ
ማነው ፡ ጽኑ ፡ ከአምላካችን ፡ ሌላ
የፈረሰ ፡ ሕይወት ፡ ጠጋኝ
ሁሉ ፡ ሲክድ ፡ ቀሪ ፡ ታማኝ
እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ለዘለዓለም ፡ ታማኝ

አዝ
ክቡር ፡ ክቡር ፡ ሃያል ፡ ክቡር
ለዘለዓለም ፡ የምትኖር
አምላካችን ፡ እግዚአብሔር (፪x)

ለዛለው ፡ ምርኩዝ ፡ ደጋፊ
የደከመን ፡ አሳራፊ
ሁሉን ፡ ታጋሽ ፡ ፍፁም ፡ ልበ ፡ ሰፊ
የመሸበት ፡ አሳዳሪ
ለተጠቃ ፡ ተቆርቋሪ
እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ለዘለዓለም ፡ ነዋሪ

አዝ
ክቡር ፡ ክቡር ፡ ሃያል ፡ ክቡር
ለዘለዓለም ፡ የምትኖር
አምላካችን ፡ እግዚአብሔር (፫x)