ራስህን ፡ አኗሪ (Rashn Anuari) - አዲስዓለም ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
አዲስዓለም ፡ አሰፋ
(Addisalem Assefa)

፭
(5)

ራስህን ፡ አኗሪ
(Rashn Anuari)

ዓ.ም. (Year): 2025
ቁጥር (Track):

፩ (1)

ርዝመት (Len.): 7:28
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስዓለም ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisalem Assefa)

እዉነት እዉነት ብቻ ምትናገረዉ
‎ ከአንደበትህ ኋላ ሁሌ ምትሰራዉ
‎ ሳይኖር ምታወራ ሳይነጋ ሌሊቱ
‎ እራስክን አንዋሪ እግዚአብሔር ብርቱ

‎ አዉርቶ ያልጨረሰህ የሚተርክህ
‎ የሚገልፅህ ልክህ የሚያዉጅህ ቀኝህ
‎ በአንተ ተመርጬ እኔም ወግ ደርሶኝ
‎ በዘመን ላይ ጎበዝ ዘመናት ላይ ኃያል አንተን አየሁኝ

‎ (ያደራረግ ባለሙያ ያሰራር አዋቂ ያጠናሀል ወይ
‎ የኔ አምላክ አዶናይ ×2
‎ የኔ አምላክ ሁሉን ቻይ ×2) ×2

‎ መሰረትህ ፅድቅና እዉነት አሃሃ እዉነት
‎ ከእጅህ ጨረር ይወጣል እሳት ኦሆሆሆ እሳት
‎ ደፍሮ ደና የሄደ ማነዉ? አሃሃሃ!ማነዉ?
‎ ከረመ እንጂ በምህረት ያንተዉ አሃሃሃ ያንተዉ

‎ ደረተ ወርቅ ራሰ በረዶ
‎ ይደገፍሀል ዘላለም ወዶ
‎ እንኳን አዉርተህ ዝም ብለህ
‎ ፍጥረት ይርዳል ከግርማህ ፊትህ
‎ ኩሩ ማዕበል እጅ ይነሳሀል
‎ ተራራ ጨሶ አለህ ይልሀል

‎ (ነበረ አትባልም ×2
‎ እግዚአብሔር ዘላለም ×2) ×2
‎ እግዚአብሔር ዘላለም ×3
‎ የኔ አምላክ ዘላለም
‎ እግዚአብሔር ዘላለም ×4

‎ የወንጌል ቁንጮ የሕይወት ሽታ
‎ የእግዚአብሔር አብ የልብ ትርታ
‎ ነቢያት ስላንተ የጮሁልህ
‎ እኔ እኔ ነኝ ያልክ አንተ አንተ ነህ

‎ የአለቅነት ጥግ የክብር ማማ
‎ ይንበረከካል ዝናህን ሲሰማ
‎ አትቀልብኝም ደጄ መተህ
‎ ነብሴም አጥንቴም ይስገዱልህ
‎ (ስምክን ጠራሁት ዳንኩኝ
‎ ምስጋናን ማለት ቻልኩኝ
‎ አደላደልከኝ ከአንተ ጋር
‎ በአባት ቀኝ እንዳልሰጋ)×2

‎ ዋጋህ ስንት ነዉ ማን ይከፍልሀል
‎ ለድርድርስ ማን ያቀርብሀል
‎ ወደድከኝ እንጂ እኔን የሆንከዉ
‎ ማንነትህንሰ ማንስ ደፈረዉ
‎ ትልቁ እግዚአብሔር ከኔ ጋር ትንሽ
‎ የቻለ አለ ወይ ስምክን ሊፈትሽ
‎ ስለሞትክልኝ ከቶ አለምድህም
‎ እፈራሀለሁ ስኖርልህ

‎ መሰረትህ ፅድቅና እዉነት አሃሃ እዉነት
‎ ከእጅህ ጨረር ይወጣል እሳት ኦሆሆሆ እሳት
‎ ደፍሮ ደና የሄደ ማነዉ? አሃሃሃ!ማነዉ?
‎ ከረመ እንጂ በምህረት ያንተዉ አሃሃሃ ያንተዉ

‎የዘላለም ነህ የዘላለም ×2
‎የምትገዛ ነህ የዘላለም ×2
‎የምትፈርድ ነህ የዘላለም ×2
‎የምትገዛ ነህ የዘላለም×2