From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation
Jump to search
|
|
አዲስዓለም ፡ አሰፋ (Addisalem Assefa)
|
|
|
|
፬ (4)
|
ጆሮዬን ፡ ልብሳ (Joroyen Libsa)
|
| ዓ.ም. (Year):
|
2018
|
| ቁጥር (Track):
|
፮ (6)
|
| ጸሐፊ (Writer):
|
አዲስዓለም ፡ አሰፋ (Addisalem AssefaProperty "Writer" has a restricted application area and cannot be used as annotation property by a user.)
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
|
የአዲስዓለም ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች (Albums by Addisalem Assefa)
|
|
|
ማነው በእግዚአብሔር እጅ የተረዳ የቆመ ሰው
ማነው ምህረቱን ያየ ፍቅሩ ብቻ የያዘው ሰው
ማነው በደግ እጆቹ የተደገፈ አቅም ሲያንሰው
ማነው እስኪ ይነሳ ከእኔ ጋራ ይቀድሰው
በእሱ ነው ነገሬ የሰመረው
በእሱ ነው የልቤ የደረሰው
በእሱ ነው ጨለማው የሸሸልኝ
በእሱ ነው መርገሙ ያላገኘኝ
በእሱ ነው ነገሬ የሰመረው
በእሱ ነው የልቤ የደረሰው
በእሱ ነው ጨለማው የሄደልኝ
በእሱ ነው መርገሙ ያላገኘኝ
ተከለከለ ጠላቴ ተከለከለ
ስሙን ስጠራው እየሱስ ቤቴን ከለለ
ሰልፉን ወሰደው ውጊያውን የህይወቴን
ሰላሜ በዛ ስሰጠው ሰውነቴን/3
ፍርዴን ሲሟገት ሲረታልኝ
ፈጣን ምስክር ሲሆንልኝ
ውስብስብ ያለው ነገሬ በእጁ ሲፈታ
ዛሬን አየሁኝ በደጉ ጌታ
ዛሬን አየሁኝ በደጉ ጌታ/4
በብዙ ካሳ በብዙ ምህረት
እግዚአብሔር ፈጥኖ የደረሰለት
እስትንፋስ ህይወት ያለሱ የሌለኝ
በእግዚአብሔር ብቻ የቆምኩ እኔ ነኝ
ማነው በእግዚአብሔር እጅ የተረዳ የቆመ ሰው
ማነው ምህረቱን ያየ ፍቅሩ ብቻ የያዘው ሰው
ማነው በደግ እጆቹ የተደገፈ አቅም ሲያንሰው
ማነው እስኪ ይነሳ ከእኔ ጋራ ይቀድሰው
በእሱ ነው ነገሬ የሰመረው
በእሱ ነው የልቤ የደረሰው
በእሱ ነው ጨለማው የሸሸልኝ
በእሱ ነው መርገሙ ያላገኘኝ
በእሱ ነው ነገሬ የሰመረው
በእሱ ነው የልቤ የደረሰው
በእሱ ነው ጨለማው የሄደልኝ
በእሱ ነው መርገሙ ያላገኘኝ
|