ኤልሻዳይ ፡ ነህ (Elshaddai Neh)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Revision as of 01:15, 22 April 2012 by Wikimezmur (talk | contribs) (አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «{{Classic | Title = ኤልሻዳይ ፡ ነህ (Elshaddai Neh) | Lyrics = <poem> :<u>አዝ</u>፦ <u>ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ</u> (፪x) ...»)
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)
Jump to navigation Jump to search

አዝ፦ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይነህ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይ

ለደካማው ፡ ሃይልህን ፡ ልትሰጥ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
መራራውን ፡ ሕይወት ፡ ልታጣፍጥ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
የደነደነውን ፡ ልብ ፡ ልትለውጥ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ

አዝ፦ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይነህ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይ

የተዘጋውን ፡ ደጅ ፡ ትከፍታለህ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
የነሃሱንም ፡ መዝጊያ ፡ ትሰብራለህ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
በጭንቀት ፡ ውስጥ ፡ ሰላም ፡ ትሆናለህ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ

አዝ፦ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይነህ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይ

ተራራውን ፡ ሜዳ ፡ ታደርጋለህ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
ሸለቆውን ፡ ውኃ ትሞላለህ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
በጨለማ ፡ ብርሃን ፡ ትሆናለህ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ

አዝ፦ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይነህ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይ

ከፋንድያ ፡ ከአመድ ፡ ታነሳለህ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
በግ ፡ ጠባቂን ፡ ንጉሥ ፡ ታደርጋለህ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
በመቶ ፡ አመት ፡ ልጅን ፡ ትሰጣለህ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ

አዝ፦ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይነህ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይ

ሰማይንም ፡ ልትለካ ፡ በስንዝር ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
ውሆችንም ፡ በእፍኝህ ፡ ልትሰፍር ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ

አዝ፦ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይነህ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይ

መራራውን ፡ ሕይወት ፡ ልታጣፍጥ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
የተዘጋን ፡ ማህጸን ፡ ልትከፍት ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
መካኒቷን ፡ በልጅ ፡ ልትባርክ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ

አዝ፦ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይነህ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይ