ቅዱስ ፡ ቃሉን ፡ የሚሰሙ (Qedus Qalun Yemisemu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Revision as of 18:06, 3 May 2014 by Redat (talk | contribs) (አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ « {{Classic |ርዕስ=ቅዱስ ፡ ቃሉን ፡ የሚሰሙ |Title=Qedus Qalun Yemisemu |ቋንቋ=አማርኛ |Language=Amharic |Lyrics=<poem> ቅዱስ ...»)
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)
Jump to navigation Jump to search

ቅዱስ ፡ ቃሉን ፡ የሚሰሙ
አምላክን ፡ የሚወዱ
ታዘው ፡ ለቅዱስ ፡ ፍቃዱ
ለጌታ ፡ የሚለፉ
በመንፈሱ ፡ የሚመሩ
በእውነት ፡ ብፁዓን ፡ ሆኑ
መንግሥቱንም ፡ ሊወርሱ

እምነታቸው ፡ ድል ፡ ሊነሳ
ጠብ ፡ ሁከት ፡ በሚገዛ
ፍቅራቸው ፡ ደምቆ ፡ ሊነድድ
ፍቅር ፡ በዓለም ፡ ሲበርድ
የተስፋቸውም ፡ መሠረት
ፀንቷል ፡ እንደ ፡ አለት
በሞት ፡ ሆነ ፡ በሕይወት

ድሙቅ ፡ ጩራ ፡ ከአብ ፡ ግርማ
ይውረድ ፡ በምድር ፡ ዙርያ
ተንጀርግጐ ፡ ሊያፈራ
ቸርነት ፡ ሰላም ፡ ደስታ
በግርማ ፡ የምታጋባ
ይህች ፡ ምድር ፡ ትሁን ፡ ለእኛ
ሰማያዊ ፡ መግቢያ