Tesfaye Gabisso/Yenazretu Eyesus/Bewnet Asadegen

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Revision as of 21:48, 9 August 2026 by Serategna (talk | contribs) (Add Ethiopic word separator ፡ (space+፡+space format) between Ethiopic words)
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)
Jump to navigation Jump to search

ዘማሪ ፡ ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ርዕስ ፡ በእውነት ፡ አሳድገ አልበም ፡ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ

አዝ በእውነት ፡ አሳድገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በፍቅር

በከንቱ ፡ መታበያችን ፡ ይቅር

በእውነት ፡ አሳድገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በፍቅር


በክርስትናችን ፡ ዕድሜ ፡ ቆጥረን

በልምምዳችን ፡ ኮርተን

በትህትና ፡ መማሩ ፡ ቀረና

እድገታችን ፡ ቆመ ፡ ታበይንና


አዝ በእውነት ፡ አሳድገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በፍቅር

በከንቱ ፡ መታበያችን ፡ ይቅር

በእውነት ፡ አሳድገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በፍቅር


ባስተያየታችን ፡ ጠቢባን ፡ ነን

ትንኝን ፡ እናጠራለን

ራሳችንን ፡ ማንጻት ፡ ሳይቻለን

የሌላውን ፡ ጉድፍ ፡ እናያለን


አዝ በእውነት ፡ አሳድገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በፍቅር

በከንቱ ፡ መታበያችን ፡ ይቅር

በእውነት ፡ አሳድገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በፍቅር


ማደጋችንን ፡ እዩልን ፡ እያልን

በከንቱም ፡ እየታበይን

አንተንም ፡ በዚህ ፡ እያሳዘንን

ሳይታወቀን ፡ ስንቶችን ፡ ጐዳን


አዝ በእውነት ፡ አሳድገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በፍቅር

በከንቱ ፡ መታበያችን ፡ ይቅር

በእውነት ፡ አሳድገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በፍቅር


እንደ ፡ ሕጻናት ፡ የዋሆች ፡ አርገን

ንጹህ ፡ ልብን ፡ መልስልን

ዓይናችንን ፡ እየገለጥህ

አንተው ፡ አመላልሰን ፡ በብርሃንህ


አዝ በእውነት ፡ አሳድገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በፍቅር

በከንቱ ፡ መታበያችን ፡ ይቅር

በእውነት ፡ አሳድገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በፍቅር


በቃል ፡ በስርአት ፡ ሙታን ፡ ሆነን

በፍቅር ፡ እየታነፅን

በእውነት ፡ እንደግ ፡ ወደ ፡ ኢየሱስ

እየታበይን ፡ እንደምን ፡ እንነስ


አዝ በእውነት ፡ አሳድገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በፍቅር

በከንቱ ፡ መታበያችን ፡ ይቅር

በእውነት ፡ አሳድገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በፍቅር