ክብርን ፡ እንሰጣለን (Keberen Ensetalen) - ኤልያስ ፡ አብጤ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Revision as of 15:51, 6 August 2018 by 73.206.223.127 (talk) (አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ « {{Lyrics |ዘማሪ=ኤልያስ ፡ አብጤ |Artist=Elias Abte |ርዕስ=ክብርን ፡ እንሰጣለን |Title=Keberen Ensetalen |አልበም=የሚ...»)
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)
Jump to navigation Jump to search

ልባችንን ፡ ከእጃችን ፡ ጋር
በሰማይ ፡ ወዳለው ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር
እናነሳለን ፡ ክብርንም ፡ እንሰጣለን
እናመልካለን ፡ በፊቱ ፡ እንሰግዳለን

ሰማይ ፡ ዝፋንህ ፡ ነው ፡ መቀመጫህ
ምድርም ፡ ለእግሮችህ ፡ መርገጫህ
ለትልቅነትህ ፡ ወሰን ፡ ነህ ፡ የሌለህ
ሰማያትንም ፡ በስንዝር ፡ የለካህ
እንሰግዳለን ፡ ለአንተ ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ጌታ

ልባችንን ፡ ከእጃችን ፡ ጋር
በሰማይ ፡ ወዳለው ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር
እናነሳለን ፡ ክብርንም ፡ እንሰጣለን
እናመልካለን ፡ በፊቱ ፡ እንሰግዳለን

እስትንፋሽን ፡ ለሙታን ፡ ትሠጣለህ
በባዶ ፡ ሸለቆ ፡ ውሃን ፡ ትሞላለህ
ጥበብህን ፡ ችሎታህን ፡ ማን ፡ ይለካዋል
ያልነበርን ፡ እንደምታኖር ፡ አውቀዋል
ከፍ ፡ ያልከው ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ ይገባሃል

ልባችንን ፡ ከእጃችን ፡ ጋር
በሰማይ ፡ ወዳለው ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር
እናነሳለን ፡ ክብርንም ፡ እንሰጣለን
እናመልካለን ፡ በፊቱ ፡ እንሰግዳለን

እንዲበላ ፡ እንዲጠጣ ፡ ለራሱ ፡ እንዲኖር
ብቻ ፡ አልነበርም ፡ ሰውን ፡ በእጅህ ፡ መስራት
እንዲያመልክህ ፡ በታላቅነት ፡ እንዲያከብርህ
መሆኑን ፡ ተረድቻለሁ ፡ እኔን ፡ መፍጠርህ
ታላቅ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ክብር ፡ ይሁንልህ

ልባችንን ፡ ከእጃችን ፡ ጋር
በሰማይ ፡ ወዳለው ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር
እናነሳለን ፡ ክብርንም ፡ እንሰጣለን
እናመልካለን ፡ በፊቱ ፡ እንሰግዳለን