WikiMezmur: Mezmur Lyrics:Zion Girma

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Revision as of 21:50, 9 August 2026 by Serategna (talk | contribs) (Add Ethiopic word separator ፡ (space+፡+space format) between Ethiopic words)
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)
Jump to navigation Jump to search

ታሪክን ፡ ሰራና፤ ታሪኬን ፡ ለወጠው እስኪ ፡ ጌታዬን ፡ ላመስግነው/3/

ከአዳምና ፡ ሔዋን ፡ በወርስኩት ፡ ሓጥያት ገና ፡ ከፍጥረቴ፤ ሳለሁ ፡ የቁጣ ፡ ልጅ የጎልጎታ ፡ ፍቅር፤ ህይወቴን ፡ ቀየረው መራራውን ፡ ሁሉ ፡ በጣፋጭ ፡ ለወጠው አዝ በሃጥያቴ ፡ ብዛት፤ የሞት ፡ ፍርድ ፡ ሲገባኝ ለኔ ፡ ሲል ፡ እየሱሴ፤ ህይወቱን ፡ ሰዋልኝ ከጨለማ ፡ አውጥቶ ፡ አረገኝ ፡ ገንዘቡ በቀራንዮ ፡ ላይ ፡ ተፈፀመ ፡ ብሎ አዝ ኑሮ ፡ አልሆን ፡ ብሎኝ፤ ግራ ፡ ተጋብቼ ነፍሴ ፡ ተጎሳቁላ ፡ እጅግ ፡ ተጨንቄ ለሞቱ ፡ አጥንቶች ፡ እስትንፋስ ፡ የሚሰጠው የናዝሬቱ ፡ እየሱስ፤ ታሪኬን ፡ ለወጠው አዝ የታሪክ ፡ ባለቤት ፡ የሆነው ፡ እየሱስ የድሃ ፡ አደግ ፡ አባት፤ ማንንም ፡ የማይንቅ ዛሬም ፡ በኛ ፡ ዘመን፤ ይሰራል ፡ ታሪክን እየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የሚያሸንፍ ፡ ሁሉን