ተመስገን ፡ ጌታዬ (Temesgen Gietayie)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Revision as of 02:11, 16 April 2012 by Wikimezmur (talk | contribs) (አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «{{Classic | Title = ተመስገን ፡ ጌታዬ (Temesgen Gietayie) | Lyrics = <poem> :<u>አዝ</u>፦ ተመስገን ፡ ጌታዬ ::ክብር ፡ ገናና...»)
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)
Jump to navigation Jump to search

አዝ፦ ተመስገን ፡ ጌታዬ
ክብር ፡ ገናናነት ፡ ለስምህ ፡ ይሁን
ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ
ክብር ፡ ገናናነት ፡ ለስምህ ፡ ይሁን

በግለት ፡ እንዲቆይ ፡ ሳይደክም ፡ ጉልበቴ
ኃይልህን ፡ አስታጠቅኸኝ ፡ ከላይ ፡ መድሃኒቴ
በብዙ ፡ ውሽንፍር ፡ ቢያጥለቀልቀኝ ፡ ጐርፉ
ጠላቶች ፡ በአንተ ፡ ስም ፡ ሁሉም ፡ ተሸነፉ

አዝ፦ ተመስገን ፡ ጌታዬ
ክብር ፡ ገናናነት ፡ ለስምህ ፡ ይሁን
ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ
ክብር ፡ ገናናነት ፡ ለስምህ ፡ ይሁን

የኑሮዬ ፡ ተገን ፡ ክብሬ ፡ መከታዬ
ኃይሌም ፡ ይታደሳል ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ተድላዬ
ማዕበሉ ፡ ተነስቶ ፡ ሊያሰጥመኝ ፡ ቢቃጣ
በገሃድ ፡ አያለሁ ፡ ረዳቴ ፡ ስትመጣ

አዝ፦ ተመስገን ፡ ጌታዬ
ክብር ፡ ገናናነት ፡ ለስምህ ፡ ይሁን
ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ
ክብር ፡ ገናናነት ፡ ለስምህ ፡ ይሁን

የእግዚአብሔር ፡ ቸርነት ፡ አያልቅም ፡ ቢቆጠር
ነነዌም ፡ ብትሰራ ፡ ኃጢአት ፡ በማዘውተር
አምላክም ፡ አስቦ ፡ እነርሱን ፡ ለመምከር
አዘዘው ፡ ዮናስን ፡ ለህዝቡ ፡ እንዲናገር

አዝ፦ ተመስገን ፡ ጌታዬ
ክብር ፡ ገናናነት ፡ ለስምህ ፡ ይሁን
ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ
ክብር ፡ ገናናነት ፡ ለስምህ ፡ ይሁን