ድካም ፡ ይዞኛል (Dekam Yezognal)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Revision as of 03:12, 21 September 2013 by Wikimezmur (talk | contribs) (አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «{{Classic | Title = ድካም ፡ ይዞኛል (Dekam Yezognal) | Lyrics = <poem> :<u>አዝ</u>፦ እኔን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ድካም ፡ ይዞኛ...»)
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)
Jump to navigation Jump to search

አዝ፦ እኔን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ድካም ፡ ይዞኛል
ድምጼንም ፡ ላሰማህ ፡ አቅቶኛል
ወድቄአለሁኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንሳኝ
እባክህ ፡ ሕይወቴን ፡ ለውጥልኝ

1. ቃልህን ፡ ለማንበብ ፡ ዐይኔ ፡ ታወረ
ሳልጸልይ ፡ ጉልበቴ ፡ ታሰረ
አንተን ፡ እንዳላስብ ፡ አዕምሮዬ ፡ ዛለ
እግሬም ፡ ወደ ፡ ጥፋት ፡ ኮበለለ

አዝ፦ እኔን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ድካም ፡ ይዞኛል
ድምጼንም ፡ ላሰማህ ፡ አቅቶኛል
ወድቄአለሁኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንሳኝ
እባክህ ፡ ሕይወቴን ፡ ለውጥልኝ

2. ጠፋሁኝ ፡ ጌታ ፡ ካልደረስክልኝ
ዓለም ፡ እንደ ፡ ጐርፍ ፡ እንከባለለኝ
በኀጢአት ፡ ባሕር ፡ ልሰጥም ፡ ነውና
ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ ፡ እጄን ፡ ያዘኝ

አዝ፦ አትጨክን ፡ ጌታ ፡ በእኔ ፡ በልጅህ
አውቃለሁኝና ፡ ጉድለቴን
ጌታ ፡ ሆይ ፡ አሁን ፡ ኀጢአቴን ፡ ማረኝ
የምመራበትን ፡ ብርሃን ፡ ስጠኝ

3. አየሁ ፡ ጌታዬን ፡ ወዲህ ፡ ሲመጣ
እኔን ፡ ከጥፋት ፡ ሊያወጣ
እጁን ፡ ላከልኝ ፡ ፍፁም ፡ አዳነኝ
ከእንግዲህስ ፡ ከጌታዬ ፡ ጋር ፡ ነኝ

አዝ፦ ፍፁም ፡ ቸል ፡ አልልም ፡ እርሱን ፡ ስከተል
እኔን ፡ ለመውሰድ ፡ ስለሚያስብ
መስቀሉ ፡ ለእኔ ፡ ቢከብደኝ ፡ እንኳ
ፍፁም ፡ ለመሸከም ፡ አልቦዝንም