Agegnehu Yideg/Bezu Yehonkelegn/Mesgana Mesgana

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Revision as of 21:48, 9 August 2026 by Serategna (talk | contribs) (Add Ethiopic word separator ፡ (space+፡+space format) between Ethiopic words)
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)
Jump to navigation Jump to search


የውለታህን ፡ ልክ ፡ ቆጥሬ ፡ ቆጥሬ
መጨረስ ፡ አልቻልኩም ፡ ለአሕዛብ ፡ ተናግሬ
ያደረክልኝ ፡ ቆጥሬ ፡ ቆጥሬ
መጨረስ ፡ አልችልም ፡ በቤትህ ፡ ዘመሬ
ያደረክልኝ ፡ ቆጥሬ ፡ ቆጥሬ
መጨረስ ፡ አልችልም ፡ ለአሕዛብ ፡ ተናግሬ

ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ክብር (፪x) ለአምላካችን ፡ ለእግዚአብሔር (፪x

ኃጥያተኞች ፡ ሳለን ፡ እግዚአብሔር ፡ አሰበን ከፋንዲያ ፡ ላይም ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ አረገን በሕይወት ፡ መዝገብ ፡ ላይ ፡ ሥማችንን ፡ ጻፈው የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው በሕይወት ፡ መዝገብ ፡ ላይ ፡ ሥማችንን ፡ ጻፈው የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው። አዝ ኢየሱስ ፡ እረኛችን ፡ ጠባቂያችን ፡ ሆኗል በሞት ፡ ጥላም ፡ ብንሄድ ፡ ምንድን ፡ ያስፈራናል በለመለምው ፡ መስክ ፡ በእረፍት ፡ ውኃ ፡ ዘንድ ሁሌ ፡ ይመራናል ፡ ወደ ፡ እውነት ፡ መንገድ። (፪x)

አዕምሮን ፡ የሚያልፍ ፡ ሰላሙን ፡ ሰጥቶናል በጌታ ፡ በኢየሱስ ፡ ሁሌ ፡ ደስ ፡ ይለናል ምድር ፡ ብትናውጥ ፡ አንዳች ፡ አንሆንም የመረጠን ፡ አምላክ/ኢየሱስ/ፈጽሞ ፡ አይተወንም (፪x) አዝ እግዚአብሔር ፡ ከላይ ፡ በድንቅ ፡ ጐብኝቶናል በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ኃይል ፡ በእሳት ፡ አጥምቆናል በመከራም ፡ ጊዜ ፡ እንደሰታለን እንደ ፡ ዘንባባ ፡ ዛፍ ፡ እንለመልማለን በመከራም ፡ ጊዜ ፡ እንደሰታለን በሽምግልናችን ፡ እንለመልማለን።

ላመስግነው 3x ጌታ ፡ ፍጹም ፡ ወደር ፡ የለው ላመስግነው 3x ውዴ ፡ ፍጹም ፡ ወደር ፡ የለው ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው 2x እረ ፡ ማነው ፡ ማነው ፡ እሱን ፡ የሚመስለው ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው 2x እረ ፡ ማነው ፡ ማነው ፡ ክብሩን ፡ የሚችለው ላመስግነው 3x ጌታ ፡ ፍጹም ፡ ወደር ፡ የለው [[[1]]]

  1. ↑ ስዕል:Agegnhu|thumb|jk