ፍቅሩ ፡ የማያቋርጥ ፡ ጅረት ፡ ነው (Feqeru Yemayaquaret Jeret New)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Revision as of 04:03, 21 September 2013 by Wikimezmur (talk | contribs)
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)
Jump to navigation Jump to search

1. ፍቅርን ፡ ሳስባት ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስን ፡ አልማለሁ
መላ ፡ አካላቷን ፡ አየዋለሁ
ትርጉሟን ፡ በውስጤ ፡ እረዳለሁ
ለፍቅር ፡ ትርጉም ፡
እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ የለም

አዝ፦ ፍቅሩ ፡ የማያቋርጥ ፡ ጅረት ፡ ነው
አጥንትን ፡ ዘልቆ ፡ የሚሰማ
ልዩ ፡ ጣዕምም ፡ የሞላው
የብርታት ፡ ቅኔ ፡ የሚያሰማ

2. ነፍስን ፡ ከመስጠት ፡ የበለጠ ፡ መውደድ ፡ የለም
ይህቺ ፡ ናትና ፡ ፍቅርም
ብርሃን ፡ የሆነች ፡ ለዚህ ፡ ዓለም
ፍቅርን ፡ ለማይት
ኢየሱስን ፡ መመልከት

አዝ፦ ፍቅሩ ፡ የማያቋርጥ ፡ ጅረት ፡ ነው
አጥንትን ፡ ዘልቆ ፡ የሚሰማ
ልዩ ፡ ጣዕምም ፡ የሞላው
የብርታት ፡ ቅኔ ፡ የሚያሰማ

3. በወልድ ፡ ልብ ፡ ውስጥ ፡ ያለች ፡ ፍቅር ፡ ነች ፡ ፍጹሚቱ
የገለጸልን ፡ በሞቱ
ያልተለወጠች ፡ በእርዛቱ
ፍቅርን ፡ ለመቅመስ
በኢየሱስ ፡ መታደስ

አዝ፦ ፍቅሩ ፡ የማያቋርጥ ፡ ጅረት ፡ ነው
አጥንትን ፡ ዘልቆ ፡ የሚሰማ
ልዩ ፡ ጣዕምም ፡ የሞላው
የብርታት ፡ ቅኔ ፡ የሚያሰማ