እግዚአብሔር ፡ ኃያል (Egziabhier Hayal)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Revision as of 15:52, 23 April 2012 by Wikimezmur (talk | contribs) (አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «{{Classic | Title = እግዚአብሔር ፡ ኃያል (Egziabhier Hayal) | Lyrics = <poem> :<u>አዝ</u>፦ እግዚአብሔር ፡ ኃያል ፡ በሰል...»)
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)
Jump to navigation Jump to search

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ኃያል ፡ በሰልፍም ፡ ደግሞ ፡ ኃያል
ከቶ ፡ እስከዛሬ ፡ በማን ፡ ተረቶ ፡ ያውቃል

ሕዝቡን ፡ ከልሎ ፡ የሚዋጋ ፡ ለጠላት ፡ ዛቻ ፡ የማይሰጋ
ብድራቱን ፡ መላሽ ፡ የእኛ ፡ አምላክ
ይረታ ፡ እንጂ ፡ መረታትን ፡ አያውቅ (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ኃያል ፡ በሰልፍም ፡ ደግሞ ፡ ኃያል
ከቶ ፡ እስከዛሬ ፡ በማን ፡ ተረቶ ፡ ያውቃል

የእምነት ፡ ባለድል ፡ ሳይጸጸት
ጌታውን ፡ አምኖ ፡ ሳያፍርበት
ለተስፋውም ፡ ለብሶ ፡ ሰንሰለት
ሕይወቱን ፡ ሰጥቷል ፡ ሳይሰስት (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ኃያል ፡ በሰልፍም ፡ ደግሞ ፡ ኃያል
ከቶ ፡ እስከዛሬ ፡ በማን ፡ ተረቶ ፡ ያውቃል

አንተም ፡ በኃይሉ ፡ ድል ፡ ነስተህ
በእቶን ፡ ተፈትነህ ፡ ነጥረህ
ለመንግሥቱ ፡ ብቁ ፡ ሆነህ
እንድትወጣ ፡ ጌታ ፡ ይርዳህ (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ኃያል ፡ በሰልፍም ፡ ደግሞ ፡ ኃያል
ከቶ ፡ እስከዛሬ ፡ በማን ፡ ተረቶ ፡ ያውቃል

ያን ፡ ጊዜ ፡ ተዋግቶ ፡ የረታ
የጠላቱን ፡ ጅማት ፡ የፈታ
በጽኑ ፡ አመታት ፡ የሚመታ
ሁሉን ፡ የሚችል ፡ የድል ፡ ጌታ (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ኃያል ፡ በሰልፍም ፡ ደግሞ ፡ ኃያል
ከቶ ፡ እስከዛሬ ፡ በማን ፡ ተረቶ ፡ ያውቃል