በክብር ፡ ከፍ ፡ ብሎአልና (Bekeber Kef Beloalena)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Revision as of 13:39, 14 April 2012 by Wikimezmur (talk | contribs) (አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «{{Classic | Title = በክብር ፡ ከፍ ፡ ብሎአልና (Bekeber Kef Beloalena) | Lyrics = <poem> :<u>አዝ</u>፦ በክብር ፡ ከፍ ፡ ብሎአ...»)
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)
Jump to navigation Jump to search

አዝ፦ በክብር ፡ ከፍ ፡ ብሎአልና
እንዘምር ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ምሥጋና (፪x)

ጠላት ፡ ሊያጠቃን ፡ በብርቱ ፡ ሲሮጥ
ኤርትራ ፡ ሞልቶ ፡ ልባችን ፡ ሲቀልጥ
የእኛማ ፡ ነገር ፡ አበቃ ፡ ስንል
ወርዶ ፡ ደረሰ ፡ አምላክ ፡ አዳነን

አዝ፦ በክብር ፡ ከፍ ፡ ብሎአልና
እንዘምር ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ምሥጋና (፪x)

እጅግ ፡ ሲመኩ ፡ በፈረሳቸው
አላመለጡም ፡ ደረስንባቸው
ብለው ፡ በትዕቢት ፡ እየፎከሩ
ባሕር ፡ ዋጣቸው ፡ ሳይወጡ ፡ ቀሩ

አዝ፦ በክብር ፡ ከፍ ፡ ብሎአልና
እንዘምር ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ምሥጋና (፪x)

ጠላታችንን ፡ ከባሕር ፡ ጥሎ
ያስጨነቀንን ፡ ሁሉ ፡ አስወግዶ
ዛሬ ፡ ዝማሬ ፡ ጉልበት ፡ ሆነልን
ያ ፡ ሁሉ ፡ አልፎ ፡ መዝሙር ፡ ዘመርን

አዝ፦ በክብር ፡ ከፍ ፡ ብሎአልና
እንዘምር ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ምሥጋና (፪x)

ከዛ ፡ ባርነት ፡ ነጻ ፡ ያወጣን
ቀንበራችንን ፡ የሰበረልን
በድንቅ ፡ በተዓምር ፡ በድል ፡ የመራን
እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ለዚህ ፡ ያበቃን

አዝ፦ በክብር ፡ ከፍ ፡ ብሎአልና
እንዘምር ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ምሥጋና (፪x)