ኃይል አለ ከላይ (Hail Ale Kelay) - ቢንያም ፡ ዋለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Revision as of 18:41, 8 August 2026 by Serategna (talk | contribs) (Fix video embed: bare YouTube ID in Video param (bulk fix))
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)
Jump to navigation Jump to search
ቢንያም ፡ ዋለ
(Binyam Wale)

፫
(3)

አልበም
(ያየ ይናገር)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2017)
ቁጥር (Track):

፰ (8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቢንያም ፡ ዋለ ፡ አልበሞች
(Albums by Binyam Wale)

ኃይል አለ ከላይ*2

የደከመ ሚበረታበት
ያዘነ ሚጽናናበት
የወደቀ ሚነሣበት
የበረታው ሚቀጥልበት

ኃይል የሌለውን ረዳኸው ምንኛ
በጨለማ ቀኑ ሆነኸው ጓደኛ
ደካማው ጀግኖ በክብር ቀጠለ
ደግፎ የሚያቆም የእግዚአብሔር ኃይል አለ

በመተማመን አንተን የጠበቀ
አልቀረም ከቶ እንደ ወደቀ
ኃይሉ ታድሶ እንደ ንሥር
ድል ተቀዳጀ ቆመ በክብር

ተስፋ ለቆረጠ ለወደቀ እምነቱ
ራሱን ለቆጠረ እንደሆነ ከንቱ
ኃይልህ ከጨለማ ያወጣና ነጥቆ
በክብር ያቆመዋል ያኖራል አድምቆ

ኃይል አለ ከላይ*2

የደከመ ሚበረታበት
ያዘነ ሚጽናናበት
የወደቀ ሚነሣበት
የበረታው ሚቀጥልበት

የተፍገመገመ ሊቆም ሚፍጨረጨር
ብርታቱ ጌታ ነው የለም ከሱ በቀር
በደስታ ይዘምራል ከሐዘኑ ተጽናንቶ
ያከብረዋል አምላኩ አዲስ ምዕራፍ ከፍቶ
ኃይል አለ ከላይ*2

ሚበረታበት
ሚጽናናበት
ሚነሳበት
ሚቀጥልበት