የአብሥራ ዳዊት እና ህሊና ዳዊት (YEABSERA DAWIT AND HELINA DAWIT)



የክብር ፡ ልብሷን ፡ ለብሳ ፡ እንደቆመች ፡ ንጉሱ ፡ ፊት የወርቁንም ፡ ዘንግ ፡ እንደነካች ፡ ጥያቄዋንም ፡ እንደመለሠላት እኔም ፡ ኢየሱስን ፡ ለብሼ ፡ አብ ፡ ፊት ፡ ሞገስ ፡ አገኘሁ አብ ፡ አባት ፡ የማለት ፡ ድፍረቴ ተመለሰልኝ ፡ ወደ ፡ ሕይወቴ አባቴ ፡ የማለት ፡ እምነቴ ተመለሰልኝ ፡ ወደ ፡ ቤቴ የመማፀኛ ፡ ከተማዬ ፡ ዘልዬ ፡ የሚያመልጥበት ካሳዳጅ ፡ ከአስጨናቂዎቼ ፡ ተሸሽጌ ፡ የምገባበት እየሱስ ፡ በተባለው ፡ ድንቅ ፡ ስም ነፍሴ ፡ አርፋለች ፡ ከምንም እርሱ ፡ የከፈለውን ፡ ዋጋ አልፎ ፡ ማን ፡ ነው ፡ እኔን ፡ የሚነካ በደም ፡ የከፈለውን ፡ ዋጋ ደፍሮ ፡ ማን ፡ ነው ፡ እኔን ፡ የሚጠጋ ከሳሾቼ ፡ ብዙ ፡ ናቸው ተጨባጭ ፡ መረጃ ፡ አላቸው በሕጉ ፡ መሠረት ፡ ቢሄዱ ፡ አሳማኝ ፡ ነው ፡ ምክንያታቸው በየትኛው ፡ ቅድስትናዬ ፡ ልጋፈጥ ፡ ልቆም ፡ ለራሴ አንገት ፡ መድፋት ፡ መሸማቀቅ ፡ ዝምታ ፡ እንጂ ፡ መልሴ የቤቴ ፡ ክፍተት ፡ ሳይ ፡ ገፋው ገፍቶ ፡ ባይገባ ፡ ከደጄ የልቤ ፡ ርቀት ፡ ሳይ ፡ መልሰው ፡ ባያቅፈኝ ፡ ባይሆን ፡ ወዳጄ ሁሉም ፡ በራሱ ፡ ፈጽሞ ፡ ባይ ፡ አደረገኝኖሮ ፡ ቀና ጽድቄ ፡ ብዬ ፡ የማስቆጥረው ፡ የማሳየው ፡ ምን ፡ አለና ፍርድ ፡ ያልተዛባም ፡ ልክ ፡ እኮ ፡ ነው ተከድኖ ፡ ሳይሆን ፡ ተከፍሎ ፡ ነው በከንቱ ፡ አይደለም ፡ ደስታዬ እየሱስ ፡ ሆኖኝ ፡ ነው ፡ ይቅርታዬ ያሸነፈልሽ ፡ ተሸነፈ ፡ ጌታሽ ፡ አበቃለት ፡ ሲሉኝ የሞተውን ፡ ስጡኝ ፡ ያልኩበት ፡ ምክንያት ፡ አለኝ የኔው ፡ እንደሌላ ፡ መች ፡ ሆኖ ፡ ቀርቦ ፡ ሲያጫወተኝ ፡ ቤዛዬ ዓሣ ፡ ማጥመድ ፡ በሰው ፡ ፊት ፡ የሚወራ ፡ አይደለም ፡ ሥራዬ በኃጢአተኞች ፡ ገበታ ፡ እንዴት ፡ ይቀርባል ፡ ሲሉት እኔን ፡ ከመውደድ ፡ አልቦዘነም ፡ ከክብሩ ፡ በልጬበት ታዲያኮ ፡ አማራጭ ፡ የሌለው ፡ ሙሉ ፡ ልቡን ፡ የሰጠ ፡ ሰው ክብሩን ፡ ከመጣል ፡ ከማሸነፍ ፡ ከመውደድ ፡ ማን ፡ ሊመልሰው ፍርድ ፡ ያልተዛባም ፡ ልክ ፡ እኮ ፡ ነው ተከድኖ ፡ ሳይሆን ፡ ተከፍሎ ፡ ነው በከንቱ ፡ አይደለም ፡ ደስታዬ እየሱስ ፡ ሆኖኝ ፡ ነው ፡ ይቅርታዬ ፍርድ ፡ ያልተዛባም ፡ ልክ ፡ እኮ ፡ ነው ተከድኖ ፡ ሳይሆን ፡ ተከፍሎ ፡ ነው በከንቱ ፡ አይደለም ፡ ደስታዬ ስለሆነኝ ፡ ነው ፡ ይቅርታዬ ይቅርታዬ (*2)