Agegnehu Yideg/Hallelujah Talaq Neh/Yemechereshayie
ዓለም ፡ ስትንጫጫ ፡ ወከባ ፡ ሲበዛ
ለእኔ ፡ ግን ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ የዘለዓለም ፡ ቤዛ
መሸሸጊያዬ ፡ ነህ ፡ ይሄው ፡ አስከዛሬ
አሁንም ፡ አደራ ፡ አድርሰኝ ፡ አገሬ(፪)
መደምደሚያዬ ፡ ነህ
የመጨረሻዬ
ኢየሱሴ ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ
እየሱሴ ፡ ለኔ
እየሱሴ ፡ ለኔ (፪x)
ሰው ፡ ሁሉ ፡ ይሄዳል ፡ ወደየ ፡ አምላኩ
ስዓቱ ፡ ሲያበቃ ፡ የዚች ፡ ዓለም ፡ ልኩ
ለእኔ ፡ ግን ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ የነፍሴ ፡ ውሳኔ
ከኃጢአት ፡ ያዳንከኝ ፡ ኢየሱስ ፡ መድህኔ(፪)
አዝ
መደምደሚያዬ ፡ ነህ
የመጨረሻዬ
ኢየሱሴ ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ
እየሱሴ ፡ ለኔ
እየሱሴ ፡ ለኔ (፪x)
በጓዳዬ ፡ ያለህ ፡ አልማዜ ፡ ንብረቴ
ለሰው ፡ የማሳይህ ፡ ትምህክቴ ፡ ኩራቴ
እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ ቀን ፡ የማይለውጥህ
አነሰብኝ ፡ እኔስ ፡ እድሜዬን ፡ ብሰጥህ(፪)
መደምደሚያዬ ፡ ነህ
የመጨረሻዬ
ኢየሱሴ ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ
እየሱሴ ፡ ለኔ
እየሱሴ ፡ ለኔ (፪x)
እየመሸ ፡ ሄደ ፡ ፀሐይ ፡ ዘቀዘቀች
ነፍሴ ፡ ግን ፡ አሁንም ፡ አንተን ፡ አለወጠች
የዚህ ፡ ዓለም ፡ ክብር ፡ ሃብት ፡ ብልጽግና
ከአንተ ፡ ዓይነጥሏትም ፡ ትኖራለች ፡ ገና
አዝ
መደምደሚያዬ ፡ ነህ
የመጨረሻዬ
ኢየሱሴ ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ
እየሱሴ ፡ ለኔ
እየሱሴ ፡ ለኔ (፪x)