Agegnehu Yideg/Gieta Eko New/Nefsie Anten Alech
ዘማሪ ፡ አገኘሁ ፡ ይደግ ርዕስ ፡ ነፍሴ ፡ አንተን ፡ አለች አልበም ፡ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው
ከምድረ ፡ በዳው ፡ ኑሮ ፡ ከዛ ፡ ከቃጠሎ አንተ ፡ ነህ ፡ የታደካት ፡ ደርሰህላት ፡ ቶሎ ስለዚህም ፡ ነፍሴ ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ አለች ቀንና ፡ ሌሊት ፡ ፊትህን ፡ ፈለገች
አዝ ዋላ ፡ ወደ ፡ ውኃ ፡ ምንጭ ፡ እንደምትናፍቅ ነፍሴ ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ አለች (፬x)
ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለነፍሴ ፡ ትርጉሟ እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ የኑሮ ፡ ጣዕሟ ያለ ፡ አንተ ፡ መኖር ፡ አይሆንላትም መጠጊያ ፡ ጐጆ ፡ ሌላ ፡ የላትም
አዝ ዋላ ፡ ወደ ፡ ውኃ ፡ ምንጭ ፡ እንደምትናፍቅ ነፍሴ ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ አለች (፬x)
ባስለመድከኝ ፡ ስፍራ ፡ እጠብቅሃለሁ አንተን ፡ ካላገኘሁ ፡ መቼ ፡ እተኛለሁ ሌሊቱ ፡ ጭር ፡ ብሏል ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ተኝቷል ከአንተ ፡ ጋር ፡ መሆኑ ፡ ነፍሴ ፡ ግን ፡ አምሯታል
አዝ ዋላ ፡ ወደ ፡ ውኃ ፡ ምንጭ ፡ እንደምትናፍቅ ነፍሴ ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ አለች (፬x)
እግዚአብሔር ፡ አለቴ ፡ እመካብሃለሁ እስከ ፡ ዘለዓለሙ ፡ ተስፋ ፡ አደርግሃልሁ ምንም ፡ ሳትሰራልህ ፡ ነፍሴን ፡ ወደሃታል ለቀሪውስ ፡ ጉዞ ፡ ምንድን ፡ ያሰጋታል
በእንባ ፡ አንተኑ ፡ ደጅ ፡ ልጥና በልጅህ ፡ አትጨክንምና በእንባ ፡ አባቴን ፡ ደጅ ፡ ልጥና ሌላ ፡ የለኝምና (፪x) አትጨክንምና ፡ ሌላ ፡ የለኝምና (፬x)