Agegnehu Yideg/Bezu Yehonkelegn/Men Ehonalehu
ዘማሪ ፡ አገኘሁ ይደግ
ርዕስ ፡ ምን ፡ እሆናለሁ
አልበም ፡ ብዙ ፡ የሆንክልኝ
ምድር ፡ ስትጨነቅ ፡ ዘመኑ ፡ ሲከፋ
እኔ ፡ አንተን ፡ ይዣለሁ ፡ የዘለዓለም ፡ ተስፋ
በቤትህ ፡ አለሁኝ ፡ እስካሁን ፡ ተጉዤ
እየዘማመርኩኝ ፡ በገናዬን ፡ ይዤ
አዝ
ምን ፡ እሆናለሁ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ እሆናለሁ
ምን ፡ እሆናለሁ ፡ አንተን ፡ አግኝቻለሁ
ምን ፡ እሆናለሁ ፡ በቃ ፡ ምን ፡ እሆናለሁ
ምን ፡ እሆናለሁ ፡ ተደግፌሃለሁ (፭x)
ስለዚህ ፡ አመልክሃለሁ (፪x)
በቤትህ ፡ ምን ፡ አጥቻለሁ ፡ ገና ፡ እኖራለሁ
ማረፊያ ፡ አንተ ፡ ነህ (፫x)
ተጠለልኩ ፡ በጥላህ
ማረፊያ ፡ አንተ ፡ ነህ (፫x)
ተመካሁ ፡ በሥምህ
ምን ፡ ይዋጠኝ ፡ ብዬ ፡ ለኑሮዬ ፡ አልሰጋም
የጐደለኝ ፡ የለም ፡ አንተን ፡ ከተጠጋሁ
በሰላም ፡ ወጥቼ ፡ በሰላም ፡ አገባለሁ
ዓለም ፡ የሌላትን ፡ ሰላም ፡ አግኝቻለሁ
አዝ፦
ምን ፡ እሆናለሁ...
ምድር ፡ ስትጨነቅ ፡ ዘመኑ ፡ ሲከፋ
እኔ ፡ አንተን ፡ ይዣለሁ ፡ የዘለዓለም ፡ ተስፋ
በቤትህ ፡ አለሁኝ ፡ እስካሁን ፡ ተጉዤ
እየዘማመርኩኝ ፡ በገናዬን ፡ ይዤ
አዝ፦
ምን ፡ እሆናለሁ...
ምን ፡ ይዋጠኝ ፡ ብዬ ፡ ለኑሮዬ ፡ አልሰጋም
የጐደለኝ ፡ የለም ፡ አንተን ፡ ከተጠጋሁ
በሰላም ፡ ወጥቼ ፡ በሰላም ፡ አገባለሁ
ዓለም ፡ የሌላትን ፡ ሰላም ፡ አግኝቻለሁ
የዚህ ፡ ዓለም ፡ ሰዎች ፡ በሚያልፈው ፡ ሲመኩ
የሰውን ፡ ማንነት ፡ በገንዘብ ፡ ሲለኩ
እኔ ፡ ግን ፡ በአንተ ፡ ልመካ ፡ በማታልፈው ፡ ጌታ
ስለምታዋጣኝ ፡ የማታ ፡ ማታ
አዝ፦
ምን ፡ እሆናለሁ ፡ ጌታ