ምሥጋና መዘምራን (የኢትዮጵያ ወጌላዊት ምሥጋና)
ያሻገረኝ በድል ያወጣኝ
ሰባራውን ድልድይ ገጥሞ ያሳለፈኝ
የረዳኝ እግዚአብሔር ነው
ከማንም ቀድሞ ለእኔ የደረሰው (2X)
አሳዳጆቼ ስማማሉብኝ ሞቴን ተመኝተው ሲሳለቁብኝ ቅናቱ ከሰማይ ከመቅደሱ ወጣ በቁጣው በትር ጠላቶቼን መታ
ሁሉን የሚችል አምላክ ጥላ ሆነኝ በጠላቶቼም ፊት ከዘይቱ ቀባኝ በማጽናናቱ ዛሬ ደስ አሰኘኝ የጠላቴን ሞት በዓይኖቼ አሳየኝ
ከእንግዲህ በቃን ትካዜ ወድቋል ሁሉን በሚችል አምላክ ላይ አርፏል በጌታዬ አሁን ወጥቼ እገባለሁ የሰራልኝም ታሪክ አወራለሁ