ሄለን እምሩ (ሄሊ)
ማነው ፡ ያልታሰብ ፡ ያልተረዳ ፡ ባንተ
ዝም ፡ ብለህ ፡ ያለፍከው ፡ ጨልሞበት ፡ አይተህ
ማነው ፡ ያልመክርከው ፡ ያልሆንክልት ፡ አባት
ክማበል ፡ አምልጦ ፡ ያልዳነ ፡ ከእሳት
ሰምቼ ፡ ነብረ ፡ ፍቅር ፡ ነህ ፡ እያሉ
በቃላት ፡ ሊገልጡህ ፡ ሲያንሱ ፡ ሲጥሉ
በኔ ፡ ደርሶ ፡ አየሁት ፡ በልጦ ፡ ከሰማሁት
የፍቅር ፡ ልብህን ፡ ክልቤ ፡ ወደድኩት
ማን ፡ አለ ፡ ያዘነ ፡ አድርገኸው ፡ ባዳ ሁሉን ፡ ትቶ ፡ መጥቶ ፡ ባንተ ፡ የተጎዳ ማን ፡ ሆን ፡ ባይተዋር ፡ አንተን ፡ ብሎ ፡ መቶ ቆሞ ፡ መሄድ ፡ ቻል ፡ ከፍቅርህ ፡ ጠጥቶ
ዳካማው ፡ ታስቦ ፡ ፅኑ ፡ ሐያል ፡ ተባል
ተባብረው ፡ የጣሉት ፡ ባንተ ፡ ክብር ፡ አየ
ያሳደደህን ፡ ሰው ፡ መቼ ፡ ተባቀልከው
ይልቅ ፡ ሰው ፡ አድርገህ ፡ ስንቱን ፡ አከበርከው
ሰው ፡ ሁሉ ፡ የረሳው ፡ ፊቱን ፡ ያዞረብት ባንተ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ እንዲህ ፡ ያማረብት ስንቱን ራራህለት ፡ ስንቱን ፡ አባት ፡ ሆንከው ዘመድ ፡ የለኝ ፡ ላለው ፡ ስንቱን ፡ ተዛመድከው
ኢየሱስ ፡ የሚባል ፡ አንድ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝ
ሰው ፡ በራቀኝ ፡ ጊዜ ፡ እየቀረበኝ
አይዞሽ ፡ ልጄ ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ አለሁ ፡ እያለኝ
ሰብስቦ ፡ የያዛኝ ፡ አባት ፡ የሆነኝ
ክቤት ፡ ወዲት ፡ እሄዳልሁ ዘላለም ፡ ቤቴ ፡ ባንተ ፡ እጅ ፡ ነው ስለዚህ ፡ ጌታ ፡ አንተው ፡ ምራኝ ከጆችህ ፡ ምንም ፡ አይለየኝ አንተ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ እረኛ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የማትተኛ አንተ ፡ ነህ ፡ የኔ ፡ መሪዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ከሞት ፡ ያዳንከኝ